ስለ ብልፅግና ፓርቲ
አላማዎች
•
ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ቅቡልነት ያለው፣ ዘላቂ ሀገረ መንግሥት መገንባት
•
ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ሥርዓት መገንባት
•
ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያሰፍን ማኅበራዊ ልማትን ማረጋገጥ
•
ሀገራዊ ክብርንና ጥቅምን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት ማካሄድ
መርሆዎች
ሕዝባዊነት
ዴሞክራሲያዊነት
የሕግ የበላይነት
ልማትና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት
ተግባራዊ እውነታ
ሀገራዊ አንድነትና ኅብረ ብሔራዊነት
እሴቶች
ኅብረ ሀገራዊ አንድነት
የዜጎች ክብር
ፍትህ

ከ5ኛው መደበኛ ጉባኤ ጀምሮ ሲነሳ የቆየው የኢህአዴግ የውህደት ጉዳይ በሀዋሳው የኢህአዴግ 11ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ዘግይቷል በሚል ተገምግሞ ወደ ፈጣን ተግባር እንዲገባ በጉባኤው ተሳታፊ ተወሰነ፡፡ በመሆኑም የውህደቱን ስራ በምን መልኩ መከናወን እንዳለበት ኃላፊነት የወሰደው የኢህአዴግ ምክር ቤት ማከናወን የነበረበትን ቀሪ ተግባራት አከናውኖ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቀረበ፡፡ ህዳር 6 ቀን 2012 ዓ.ም የኢሕአዴግ ሥራ አሥፈጻሚ ኮሚቴ ተሰብስቦ ውህደቱን በ27 አብላጫና በ6 የተቃውሞ ድምፅ አጸደቀ፡፡ህዳር 7ቀንም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በውህድ ፓርቲው ረቂቅ ፕሮግራም ላይ ተወያይቶ ረቂቁን ለኢህአዴግ ም/ቤት መራ፡፡ ህዳር 9ቀን የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ “ብልፅግና ፓርቲ” የሚለው ስያሜ ለኢህአዴግ ምክር ቤት እንዲቀርብ ከስምምነት ላይ ደረሰ፡፡ ህዳር 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የኢሕአዴግ ምክር ቤት (ከህወሓት ውጭ) ውሕደቱን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ፡፡ ህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም. የአዲሱን ፓርቲ የወደፊት አቅጣጫ ያመለከተ መግለጫ ወጣ፡፡

- ፓርቲውን ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተቀብሎ በጽናት ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ፣
- መልካም ስነ ምግባር ያለውና በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያለው፣
- በህብረ ብሄራዊነት እና በሀገራዊ አንድነት ላይ ፅኑ አቋም ያለውና ዋልታ ረገጥ አመለካከትና ተግባሮችን በፅናት የሚታገል፣
- ዜጎችንና ህዝቦችን በእኩልነት የሚያገለግል፣ የህዝብ ጥቅምን የሚያስቀድም፣ ከሙስናና ብልሹ አሰራሮች ራሱን ያራቀና ሌሎችንም የሚታገል፣
- የፓርቲውን ዕሴቶችና ዓላማዎችን ተቀብሎ የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ የሆነ፤
- በፓርቲው መመሪያ መሠረት ወርሃዊ የገንዘብ መዋጮ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
- ዕድሜው አስራ ስምንት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
- የሌላ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፣
- የፖለቲካ ድርጅት አባል የመሆን መብቱ በሕግ ያልተገፈፈ፤
- በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።

ለሰዎች ፍላጎት ይግባኝ
ዴሞክራሲያዊነት
የህግ የበላይነት
ልማት እና እኩል ተጠቃሚነት
ሀገራዊ አንድነት እና ብሄርተኝነት

ጠንካራ፣ ዴሞክራሲያዊና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ ሀገረ-መንግስት መገንባት
ልማታዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት
ሁለንተናዊ ብልፅግናን የሚያሰፍን ማህበራዊ ልማት ማረጋገጥ
ሀገራዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት ማካሄድ

ለዜጎች እና ህዝቦች ክብር
እውነት
ወንድማማችነት
የጋራ መከባበር እና መቻቻል
በልዩነት ውስጥ አንድነት

ፓርቲው የሚከተሉት ራዕዮች አሉት
ጠንካራ መንግሥት፣ ዴሞክራሲና ተቀባይነት ያላት አገር መገንባት
እኩል ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት መገንባት
አጠቃላይ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ማህበራዊ ልማት መገንባት የአገሪቱን ጥቅምና ሉዓላዊነት መሠረት ያደረገ የውጭ ፖሊሲ መቅረጽ
