Kolfe Prosperity party News

Kolfe

ፓርቲያችንን በተመለከተ ማንኛውንም መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት !!
Party message
Addis Ababa

ኮልፌ ቀራንዮ

 

መግለጫ

ኮልፌ ቀራኒዮ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ካሉት ከአስረአንዱ ክፍለ ከተሞች ውስጥ አንዱ ነው። እስከ እ.ኤ.አ 2011 ባለው መረጃ መሠረት የሕዝብ ብዛቱ 546,219 ነው።

Party News

ቃል በተግባር ፤ ሰውን ማዕከል ያደረገ ጉዞ ፤ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና!! አቅመ ደካሞችን ማዕከል ያደረገውና የሰው ተኮር ስራ ውጤት የሆኑ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ፤ ውጤታቸውም የሀገራችንን ብልፅግና ጉዞ እውን በሚያደርግ መልኩ ተጨባጭ ፣ የሚታይ፣ የሚዳሰስ የብልፅግና ስራችን ሆኖ ቀጥሏል። የአዲስ አበባ ከተማ በሰው ተኮር ስራዎቿ ሞዴል እየሆነች ሁሉንም ዜጎቻችን ማዕከል ያደረገ እና ለነዋሪዎች ምቹ ቦታዎችን በመፍጠር ለአገልግሎት እያዋለች ትገኛለች። በቅርቡ በከንቲባ አዳነች አስተባባሪነት ጥራቱን ጠብቆ ተገንብቶ ለአገልግሎት የዋለው የሴቶች የክህሎት ማበልፀግያ ላይ ይህ የልበ ብርሃን አዳሪ ትምህርት ቤትም በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ተገንብቶ የከተማ አስተዳደሩ በበላይነት እንዲያስተዳድረው መደረጉ ለከተማዋ ተደማሪ እና የሰው ተኮር ስራዎቻችንን ከፍ የሚያረግ ይሆናል። ይህ ጥራቱን ጠብቆ በፍጥነት የተጠናቀቀው ግዙፍ ፕሮጀክት ለትውልድ የሚሻገር አሻራ ሲሆን ሰው ተኮር የሆነውን የብልፅግና እሳቤያችንን የተተገበረበት እና ሁሌም ቃል በተግባር የሚለው መርሃችን የታየበት ለከተማችን ተጨማሪ ድምቀት የሆነ ስራ ነው:: ሰውን ማዕከል ያደረገው የብልፅግና ጉዞ ተጠናክሮ ይቀጥላል!! ሰናይ የስራ ሳምንት ይሁንላችሁ!

Party News

ዛሬ አቅመ ደካሞችን ማዕከል ያደረገውና የሰው ተኮር ስራ ውጤት የሆነው የሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት በመመረቁ ለቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እፈልጋለሁ። ይህ ስኬት በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተሰሩና በተሳካ ሁኔታ ለአገልግሎት የበቁ የትምህርት ቤት ግንባታዎችን ፈለግ ተከትሎ በመገንባት የተገኘ ነው። ከዚህ የዐይነ ስውራን ትምህርት ቤት ስኬት ትምህርት በመቅሰም የምንገነባቸው የከተሞቻችን መሰረታተ ልማት የአካል ጉዳት ላለባቸው ዜጎች ትኩረት የሚሰጡ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባናል። በዚህ አጋጣሚ ይህን የላቀ ትርጉም ያለው ስራ በመደገፋቸው ግርማዊት ሼካ ፋጢማ ቢንት ሙባረክን አመሰግናለሁ። ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር )

Party News

ለ2 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርም አዳዲስ አመራሮችን በመምረጥ ተጠናቀቀ!! በክ/ከተማው የሚገኙ 14 የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት መካከል በ13ቱ ሪፎርም ተካሂዷል:: በዚህም 91 የቦርድ አመራሮችእና 36 የቁጥጥር ኮሚቴዎች በአጠቃላይ 127 አመራሮች ላለፉት ዓመታት ማህበራቱን የመሩት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 81 በአዲስ መተካታቸውን እና ከተመረጡት አመራሮች ውስጥ 71 ዲግሪና ከዛ በላይ 41 ዲፕሎማ እንዲሁም ሴቶች እና ወጣቶችን ማካተት መቻሉን የህብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ደመቁ ንጉሴ ገልፀዋል። ሪፎርሙ በቀጣይም ወደ ሸማች ህብረት ስራ ባለሙያውም የሚወርድ ሲሆን አጠቃላይ ተቋሙላይ ቴክኖሎጂን መስፈፀም የሚችል የሰው ሀይል ድልድል እንደሚደረግና በሸማች ህብረት ስራ ማህበር የሚሰጡ አገልግሎቶቹን በቴክኖሎጂ ማስደገፍን ያካተተ እንደሚሆንም ተገልጿል። በሪፎርሙ ከ6460 በላይ የማህበሩ አባላት ተሳትፈውበታል።

Play Video
Play Video
Play Video

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአባላት መረጃ

አጠቃላይ አባል
0
ወንድ
0 +
ሴት
0 +
መሠረታዊ ድርጅት በተቋም ብዛት
0
ህዋስ በተቋም ብዛት
0

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሶሻል ሚዲያ መረጃ

የፓርቲው ፌስቡክ ቻናል ተከታይ
0
የፓርቲው ቲክቶክ ቻናል ተከታይ
0 +
የፓርቲው ቴሌግራም ቻናል ተከታይ
0 +
የፓርቲው ቲውተር ቻናል ተከታይ
0
የፓርቲው ዩቲዩብ ቻናል ተከታይ
0