አባል ሰለመሆን
- የፓርቲውን ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ተቀብሎ በጽናት ተግባራዊ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆነ፣
- መልካም ሥነ ምግባር ያለውና በኅብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ያለው፣
- በኅብረ ብሔራዊነት እና በሀገራዊ አንድነት ላይ ጽኑ አቋም ያለውና ዋልታ ረገጥ አመለካከትና ተግባሮችን በጽናት የሚታገል፣
- ዜጎችንና ሕዝቦችን በእኩልነት የሚያገለግል፣ የሕዝብ ጥቅምን የሚያስቀድም፣ ከሙስናና ብልሹ አሠራሮች ራሱን ያራቀና ሌሎችንም የሚታገል፣
- የፓርቲውን ዕሴቶችና ዓላማዎችን ተቀብሎ የተሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ የሆነ፤
- ወርኃዊ የገንዘብ መዋጮ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
- እድሜው አሥራ ስምንት ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ፣
- የሌላ ፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ፣
- የፖለቲካ ድርጅት አባል የመሆን መብቱ በሕግ ያልተገደብ ወይም በፍርድ ቤት ዉሳኔ ያልተገፈፈ፤
በዚህ ደንብ በተወሰነው መሠረት የሙከራ ጊዜውን የጨረሰ የፓርቲው አባል መሆን ይችላል።